Amahric Research
Amahric Research
መግቢያ
1.1 የጥናቱ ደራ
በማንኛውም ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች የተለያየ ፍላጎት፣ ዝንባሌ፣ ችሎታና ችግሮች አሏቸው፡፡ ትምህርት
ሚኒስቴር በ 1994 ዓ/ም በትምህርት ስልጠና ፖሊሲው ላይ የተመሰረተ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ስትራቴጂ ቀርፆ
ሲንቀሳቀስ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንኑ ስትራቴጂ ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦም የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት
ስትራቴጂ በአዲስ መልክ እየተቀረፀ ይታያል፡፡
ይሁን እንጂ አገራችን የትምህርት ለሁሉም ግቦችን ለማሳካት ከሚታደርገው ጥረት አኳያ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ተደራሽ
ለማድረግ አሁንም ክፍተት መኖሩ ይስታዋላል፡፡ እነዚህን ለማገዝ የሚያስችል የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ አለመደራጀት፣ የተመቻቸ
የመማሪያ አከባቢ አለመኖር፣ የመማር ችግራቸውን ለይቶ እገዛ ለመስጠት የሚያስችል የመለያና የዳሰሳ ስርዓት አለመጠናከር ዋና
ዋናዎቹ ተግዳሮቶች እንደሆኑም ይታመናል፡፡
በመሆኑም ትምህርተ ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብለው እንደችሎታቸውና ፍላጎታቸውን ለማስተናገድ ያላቸው
ፈቃደኝነት ሲገዳደራቸው ይስተዋላል፡፡
በተለያዩ አካላት የትምህርት፣ የፆታና የሞራል እገዛ በማድረግ ተማሪዎቱ ለትምህርት ያላቸው አመለካከት አወንታዊ በማድረግ
ትምህርታቸው እንዲከታተሉ የሚያደርግ ሁኔታ ይደረጋል፡፡ ትምህርት የዜጎችን ዲሞክራሲያዊ እሴቶችንና እኩልነትን ከሰብአዊ
መብት ጋር አጣምሮ ሊያስገኝ የሚችል መሳሪያ ከመሆኑም ባሻገር ድህነትን በመቀነስ ዜጎች ሁሉ በአገሪቱ የማህበራዊና
በኢኮኖሚያዊ መስኮች ተጠቃሚ እንደሆኑ የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ /ትምህርት ሚኒስቴር 1994/፡፡
ከተለያየ ባህልና አምስት ያላቸው ህብረተሰብ የመጡ ተማሪዎች በፆታ፣ በዕድሜ፣ ብፍላጎትና በትምህርት አቀባበል ልዩ ፍላጎት
ያለባቸው ናቸው፡፡ እንደመሆናቸው ያላቸው ልዩነት ግምት ውስጥ በማስገባት በእኩል የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ይፈለጋል፡፡
በተማሪዎች ላይ ያለው ልዩነት እንዳለ ሆኖ እኩል የትምህርት ዕድል በማግኘት ዘዴ አካቶ ትምህርት ይባላል፡፡
በአካቶ ትምርት የማስተማሪያ ዘዴ ሁሉም ተማሪዎች ፍላጎትና ልዩነት በመቀበል በማበረታታት የመማር ዕድል የሚያገኙበት ዘዴ
ነው፡፡ ይህን ለአካል ጉዳተኞችም የሚያጠቃልል ነው፡፡ ነገር ግን በመጠናቸው አናሳ ናቸው፡፡
የትምህርት ክልል ትምህርት ቢሮ ዘገባ (2004:3) የትምህርት አፈፃፀም ተግባር አካቶ ክልል ትግራይ እንደሚገልፀው
በ 2008 ዓ/ም ትምህርት ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስ የተያዙትን ዕቅዶች ሲገመገም በመደበኛ ትምህርት ቤት እንዲማሩ ከሚገባቸው
አካል ጉዳተኞች የትምህርት ዕድል ያገኙ 37%ብቻ ናቸው፡፡ 63% ደግሞ የትምህርት ዕድል ያላገኙ ወይም አመች ትምህርት
ቤት ባለማግኘታቸው ያቋረጡ ናቸው፡፡
በፈረደ ረዳኢ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመከታተል ከነበሩ 178 ተማሪዎች 8 የአካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡ ይህንን
እንደሚያመለክተው የተለያየ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች መማር እንደምችሉ ይጠቁማል፡፡ ነገር ግን የአካቶ ትምህርት ለሁሉም
በተግባር ምን ያህል አጋዥ እንደሆነ ፍተሻ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ የአካል ጉዳተኞች ወገኖቻችን ባላቸው ጉዳት
ያለምንም ስጋት እንድማሩ የሚደረግላቸው ድጋፍ ምን እንደሚመስል መታየት አለበት፡፡ ይህ አስመልክቶ Tirussew
( 2005፣ 6 -8) እንደገለፀው
የአካል ጉዳተኞች የሰቆቃን ምንጭ ሆኖ የሚታይ ነው፡፡ በቤተሰብ መካከልም ልዩነት የሚፈጥርና ተቀባይነት የሌለው ሆኖ
ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አካል ጉዳኞች እንደ ደካማ፣ ራእይ የሌላቸው፣ ጥገኞችና ሊማሩ እንደማይችሉ ስለሚታዩ
ከማህበራዊ ጉዳይ ገለልተኛ ሆነው ይኖራሉ፡፡
እላይ እንደተጠቀሰው በአካል ጉዳተኞች አሉታዊ አመለካከት ካለ አካል ጉዳተኞቹ ተምረው ውጤታማ የሆነ ስራ እንድሰሩ
የሚያችላቸውን ድጋፍ ለማድረግም ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፣ ብህፃኑ ላይ ያጋጠመው ጉዳት ላይም መቀበልና ማበረታታት አይኖርም፡፡
ባጠቃለይ የትምህርት አገልግሎት እንደሚከላከልም ይገመታል፡፡ አካቶ ትምህርት ግን በተማሪዎች ላይ ያለው ልዩነት በመቀበልና
በማበረታታት ትምህርት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት ዘዴ ነው፡፡ Renzaglia ( 2003: 149)” የአካቶ ትምህርት
ትምህርት ቤትና ህብረተሰብ፣ ተማሪዎች ያለምንም ልዩነት ተቀብለው እንድሳተፉ የሚያበረታታና የሚደግፍ አስተሳሰብ ነው፡፡”
ይላል፡፡
የአካቶ ትምህርት የማስተማሪያ ዘዴ ሁሉም ተማሪዎች ካላቸው ልዩነት አካል ጉዳተኞችና የትምህርት አቀበባልን ወዘተ በመማር
የግልና የጋራ ፍላጎት ውጤታማ በሆነ መንገድ በእኩል የሚያሳትፍ አቀራረብ ይከተላል፡፡ ይህ ማስተማሪያ ተማሪዎች ካላቸው
ልዩ ችግር ተስፋ እንዳይቆርጡ የሚያበለፅግ ሂደት ነው፡፡ የአካቶ የማስተማሪያ ዘዴ ጥንቃቄ ፈላጊ ነው፡፡ አፈፃፀሙ በአንድ
አካል የሚፈፀም ሳይሆን የተለያዩ አካላት የሚያስፈልጉበት ዋና ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ተማሪዎች ሁሉ
በፍላጎታቸው እኩል
አካቶ መምህራን፣ ሰራተኞች፣ አስተዳደርና ወላጆች ላለቀተሳትፎ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ተማሪዎች ችሎታቸውና እውቀታቸው
የሚያጎለብቱት ክፍል ውስጥ በመምህራን በሚከናወነው ተግባር ብቻ ሳይሆን ባጠቀላይ ድጋፍ ጭምር ነው፡፡ ወላጆች፣ ልጆቻቸው
ጥሩ ውጤት ለማምጣት መከታተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ መኮነን (1998:15) እንደሚከተለው አጠናክሮታል፡፡ ትምህርት ከቤትና
ከልጅነት ይጀምራል፡፡ በህፃናት ህይወትም እየተስፋፋ ይሄዳል፡፡ ህፃናት መማር እንድችሉ የወላጆች እርዳታ
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወላጆችና ቤተሰቦች አስፈላጊ የሆኑ መምህራን ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ ስኬታማ ለመሆን ወላጆች የሚጫወቱበት
ሚና የሚናቅ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በትምህርት ዘርፍ ስኬታማ ሊሆኑ እንደምችሉ ከፍተኛ የሆነ
አመኔታና ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተስማሚ የመማሪያ ክፍል የማደራጀት ተግባር በዋንኞነት የመምህሩ ሓላፊነት
ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ በግለ ሰብ እንደሚከበሩ ካወቁ በመካካላቸው የመከባበር ስሜት ያደብራሉ፡፡ ልዩ ፍላጎት
ያላቸው ተማሪዎች ለተጨማሪ ድጋፍ በማበረታታት ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ልዩነቱን ተቀበለውና አክብረው የመኖር ዕድል ይፈጥራል፡፡
ከአከባቢያቸው ከሚገኙ ሌሎች ህፃናት ራሳቸውና ማንነታቸው ሳይቀይሩና ሳይሰጉ ጓደኝነት ይመሰረታሉ፡፡ ወላጆች
በአካባቢያቸውም ሆነ በትምህርት ቤት በሚደረገው እንቅስቃሴና ዕቅድን እንድሳተፉ ያስችሏቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ስርዓተ ትምህርቱ የተለያየ ችግር ያለባቸውና የሌለባችው ተማሪዎች ባንድ ላይ እንዲማሩ የሚያደርግ ነው፡፡
አንድ ላይ የሚመሩተ ግን ችግር የማይፈጥር ከሆነ ነው፡፡ የትግራይ ክልል እንደጠቀሰው የአከቶ ትምህርት አፈፃፀም ወሳኙ
ትዝብት እየሆነ መጥተዋል፡፡ በተለይ የአካል ጉዳት ባላቸው ሰዎች የአካቶ ትምህርት አጠቃላይ ሁኔታ ለመፈተሽ መረጃ
በመጥቀስ እድሎችን በማቅረብ ያለመ ነው፡፡
ሰበብ ጥናት
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በ 1994 ዓ/ም ሁሉም ህፃናት በእኩል የትምህርት ዕድል የሚገኙበት ፖሊሲ ስልጠናና ትምህርት
እውን አድርገዋል፡፡ በፖሊሲ መሰረት የሁሉም ህፃናት ፍላጎት በማበረታታት የትምህርት አገልግሎት አገልግሎት በእኩል
መስጠት እንደ መብት ይታያል፡፡ ይህ አካል ጉዳተኞችም ያጠቀልላል በመሆኑም ከ 1998 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ፈላጎት /የአካቶ
ትምህርት በተግባር እንደ ትምህርት ሚኒስቴር /1991፡1/ ገልፀዋል፡፡ ይህ ሁሉም ዜጋ ጥራቱ የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ
መብት መሆኑን ይገልፃል፡፡ የአካል ጉዳተኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተማሩ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት
ጥናት የተካሄደበት ትምህርት ቤት በመማር ላይ ከነበሩ 178 ተማሪዎች 8 አካል ጉዳተኞች ነበራቸው፡፡ እንደምንገነዘበው
የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ህፃናት በአንድ ክፍል ውስጥ በማሳተፍ ዕውቀታቸወ የሚሳደጉበት መንገድ አቅጣጫን ያመለክታል፡፡
ልዩነቱ በመቀበልና በማበረታታት ሁሉም ተማሪዎች የትምህርተ ዕድል የሚያገኙበት የማስተማሪያ ዘዴ የአካቶ ትምህርተ ነው፡፡
የአካቶ ትምህርት የማስተማሪያ ዘዴ የተመቻቸ የትም/ት ቤት ሁኔታ ግብአትን በመጠቀም የሚተገበር ነው፡፡ የ rnisner
(2003:145) የአካል ጉዳት ያላቸው ተማሪዎች በአጠቃላይ ትምህርት ቤት እንዲማሩ የሚችሉበት ከማደራጀት ጀምሮ የርእሰ
መምህራን አመለካከት ወሳኝ ነው፡፡ እንዲሁም የመምህራን ሰራተኞች፣ አስተዳደር፣ የትምህርት ቤት ቁጥርን ፣ የመማሪያ
ክፍለች፣ የማስተማሪያ መሳሪያዎች ሟሟላት ለአካቶ ትምህርት መማር ማስተማር ትምህርተ ቤት የመጡ ተማሪዎች የተለያየ
እውቀትና የትምህርት አቀባበል ስላላቸው ነው፡፡ የተማሪዎቹ ልዩነት በዕለቱ ትምህት በንቃት ተሳታፊ እንዲሆኑ የአካቶ
ትምህርት የመበረታት ስልት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአካቶ ትምህርት ቅደመ ዘአገጃጀት አተገባበርን የሚታዩ ክፍቶተች እንዳሉ
ትምህርት ሚኒስቴር (1998:2) እንደሚከተለው ይገለፃል፡፡
የአካቶ ትምህርት አተገባበር ክፍተት እንዳሉት ይታያሉ፡፡ የህፃናት ፍላጎት አለማወቅ፣ የተለመደ የማስተማሪያ ዘዴ መጠቀም፣
ተማሪ ተኮር አለመጠቀም፣ በጥቅም ላይ የማይውሉ ቁሳቁሶችን አለማራቅ፣ የማጥኛ ጥግ አለማዘጋጀት፣ ተማሪዎችን ባግባቡ
ለማደራጀት የሚያስችሉ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ( Check list) አለማዘጋጀት፣ ተማሪው አስፈላጊ የሆነ የእገዛ መሳሪያ
አለመኖር፣ መምህሩ ስለአካቶ ትምህርት የማስተማሪያ ዘዴ ስልጠና አለማግኘት ብቃት ያለው የፈተና አሰራር ያለመኖር ለትምህርት
ዕድል እንቅፋቶች ናቸው፡፡ በዚህኛውን ችግር የተነሳ ትምህርት ቤትና መምህራን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ለማስተማር
ይቸገራሉ፡፡ ብቃት ያለው የፈተና አተገባበር ባለመኖሩ ለትምህርት ዕድል እንቅፋቶች ይሆናሉ፡፡ በችግሩ ምክንያት ደግሞ
ትምህርት ቤቶችና መምህራን የትምህርት ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች አካቶ ትምህርት ለማስተማር ይቸገራሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች
ከተማሪዎች ፍላጎት ጋር ከመስማማት ይልቅ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ፍላጎት ጋር እንዲስማሙ ይገደዳሉ፡፡
እላይ እንደተጠቀሰው ሀሳብ ትምህርት ቤቶች የአካቶ ትምህርት ስልት በፍልስፍና እንጂ በአተገባበር በጥንካሬ እንደማይሰሩ
ያመላክታል፡፡ የጥናቴ መነሻ ቀደም ብለው ባየነው ክፍተት የአካቶ ትምህርት አተገባበር በፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት ምን ይመስላል? የሚለው ነው ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጥናቱ ማካሄድ አስፈላጊ ነው፡፡ በተጠቀሰው
ትምህርት ቤት በትግርኛ ቋንቋ አካቶ ትምህርት በተግባር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ሁሉ ምን ያህል አጋዥ እንደሆነ በግል
ያልተቀመጠ ስለሆነ ነው፡፡
ስለዚህ የአካቶ ትምህርት አተገባበር በተገኙት መረጃዎች ፍተሻ በማድረጅ የሚታዩትን ክፍተቶች ለሟሟላት ነው፡፡ በትምህርት
ቤቱ ውስጥ ያለው አጠቃላይ የአካቶ ትምህርት ሁኔታ ለመፈተሽ አካቶ ትምህርት በተግባር ላይ ለማዋል በመረጃዎቹ መሰረት
አቅጣጫን ለማሳየት እንዲሞከር በማለት ጥናት ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሰረት ጥያቄዎች በመመለስ ያተኩራል፡፡ መምህራን፣
ተማሪዎች፣ የትምህርት ቤቱ አስተዳደሮችና ሰራተኞች የአካቶ ትምህርት በፈረደ ረዳኢ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያላቸው
ፍላጎት ምን ይመስላል፡፡ በትግርኛ ቋንቋ ትምህርት አተገባበር ምን ይመስላል ? መምህራን አካቶ ትምህርት በሚያስተምሩበት
ጊዜ የሚያጋጥማቸው ችግሮች ምን ይመስላል? የሚሉ ናቸው፡፡
በትግርኛ ቋንቋ የአካቶ ትምህርት በዘጠነኛና አስረኛ ክፍል ፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን እንደሚመስል
ለመዳሰስ ነው፡፡
3. መምህራን በትግርኛ ቋንቋ የአካቶ ትምህርት የማስተማሪያ ዘዴ አተገባበር የሚያጥማቸው ችግሮች ለመለየት
4. በትግርኛ ቋንቋ በአካቶ ትምህርት በመማር ማስተማር በተማሪዎች ላይ ያላቸው ችግር መጠቆም
ይህ ጥናት የአካቶ ትምህርት ትግርኛ ቋንቋ አተገባበር በተመረጠው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በግልፅ ለማሳየት ይሞክራል፡፡
ያጋጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ ችግሮች መፍትሄዎቻቸውን ይፈልጋሉ፡፡ እንዲሁም ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ እጥረቶች
እንዴት እንደሚፈቱ ይጠቁማል፡፡ የትምህርት ቤት ሠራተኞች በተማሪዎቻቸው ላይ ሊያጋጥሙ የምችሉ ነገሮች ግምት ውስጥ
ያስገባሉ፡፡ የማስተማሪያ መፃህፍት እንዲዘጋጁ ያግዛል፡፡ የተፃፈውን ጥናት በጥቂቱ በማሳየትና በመተንተን ለሌሎች
አጥኚዎች መሰረት ይሆናል፡፡ የአካቶ ትምህርት ጠቃሚነቱ ተሰንዶ እንዲቀመጥ ይረዳል፡፡
ይህ ጥናት ብእንዳመኾኒ ወረዳ ወስጥ ካሉ ትምህርት ቤቶች በተመረጠው ፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በትግርኛ ቋንቋ
የአካቶ ትምህርት አተገባበር በዘጠነኛ እና አስረኛ ክፍል ተተኳሪነት ያለው ነው፡፡ የአካቶ ትምህርት የማስተማሪያ ዘዴ
የተለያየ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ያቀፈ ነው፡፡ ነገር ግን በሚወስደው ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ፍላጎት ያላቸው
ተማሪዎች ሁሉ በጥናቱ ውስጥ ሊካተቱ አልቻሉም፡፡ የጥናቱ ዋና ትኩረት መምህራን፣ ሰራተኞችና አስተዳዳሪዎች አካል
ጉዳተኞች ተማሪዎች፣ የኔት ዎርክ መሪዎች ያጠቃልላል፡፡
በጥናቱ ላይ ልያግጥሙ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱት መካከል አጥኝዬ በገጠር ውስጥ የሞባይል ኔትዎርክ የማይሰራበት ቦታ
በመሆኑና መኪና በተፈለገ ጊዜ የማይገኝ በመሆኑ የጊዜ እጥረትና በተፈለገ ጊዜ ከአድቫይዘር /አማካሪ/ ጋር ለመገናኘት
አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከጥናቱ ጋር የሚዛመዱ ፅሑፎች የማግኘት እድሉ ያነሰ ይሆናል፡፡ በአካቶ
የማስተማሪያ ዘዴ የሰለጠነ ሰው ሃይል ሊታጣ ይችላል፡፡ መረጃዎችን ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የማግኘት እድሉ ዝቅተኛ
ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት ደግሞ ጥናቱን በተቀመጠለት ጊዜ ሳይልቅ ሊቀር ይችላል፡፡
ምዕራፍ ሶስት
የጥናቱ ዘዴ
ጥናቱ ትግርኛ ቋንቋ የአካቶ ትምህርት አተገባበር በዘጠነኛና አስረኛ ክፍል በፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ያተኮረ ሆኖ ችግሮችን በመለየት አካቶ ትምህርት በተግባር ላይ ለማዋል አቅጣጫን ለማግኘት እንዲረዳ ተብሎ ይህንን ጥናት
ተቀምጧል፡፡
3.1 የጥናቱ ተተኳሪነት በእንዳመኾኒ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ፈረደ ረዳኢ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
አካቶ ትምህርት በዘጠነኛ እና አስረኛ ክፍል ያቀደ ነው፡፡
በእንዳመኾኒ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብነት ሆና ተመርጣለች፡፡
ጥናቱ በ 2011 ዓ/ም በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ሁለት የትግርኛ ቋንቋ መምህራን፣ ሶስት የትምህርት ቤቱ ሠራተኞች
አስተዳደሮች፣ ስምንት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፣ ዘጠኝ የኔትዎርክ መሪ ተማሪዎች፣ በአጠቃላይ ሃያ ሁለት ሰዎች ሙሉ በሙሉ
ይሳተፋሉ፡፡ በጥናቱ ውስጥ እንዲሳተፉ የተመረጡበት ዋና ምክንያት አጠቃላይ ክፍል ውስጥ በመማር ማስተማር ላይ ያለው ምስል
የሚገልጽ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ ተብለው የተገመቱ በመሆናቸው ነው፡፡
ይህንን ጥናት ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ መረጃ መሰብሰብ የተጀመረው ጥናቱ የሚካሄድበት ትምህርት ቤት ከሚገኙ ስለአካቶ
ትምህርት አተገባበሩ ይታዘባሉ የተባሉ ሃያ ሁለት አካላት በመምረጥ ነው፡፡ የመረጃ አሰባሰብ ስልቱ እነዚህን መረጃ መስጠት
ይችላሉ ተብለው የተቀመጡ በሚከተለው መልኩ መረጃዎች በተግባር ላይ ይውላሉ፡፡
የፅሑፍ ጥያቄ መረጃዎች ከተለያዩ አካላት ለማሰባሰብ አጋዥ ሆኖ ተጠያቂዎች ደግሞ ነፃ ሆኖ የመሰላቸው ሀሳብ እንዲገልፁ
የሚረዳ ነው፡፡ አለም (1994:44) “ የፅሑፍ መጠይቅ የላቀ ጥቅሙ ብዙ ሰዎች በተወሰነ ጊዜ የተለያየ የመረጃ አቅጣጫ
መሰብሰቢያ ሆኖ ይገኛል ይላል”፡፡ በዚህኛውም መሰረት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ስምንት ዝግ፣ ሶስት ክፍት ስምንት
ለመምህራን፣ ለሰራተኞችና አስተዳደሮች፣ አምስት በአጠቀላይ ሃያ አራት ጥያቄዎች በማዘጋጀት ከተመረጡት መሳያ ይህንን ጥናት
መረጃዎችን ይሰበሰባል፡፡
3.3.2 ቃለ መጠይቅ
የመረጃ አሰባሰብ በዋናነት የተከናወነው መረጃ ሰጪዎች እስካሉበት በመሄድ ሲሆን በሌላ በኩል ቀደም ብሎ ለመግለፅ
እንደተሞከረው በምህርት ቤት፣ በኔትዎርክ መሪዎች፣ በትምህርት ቤት ሰራተኞችና፣ ርእሳነ መምህራን ያመለክታል፣ ይህንን
ጠያቂና ተጠያቂ በአካል ተገናኝተው በቃል መረጃ የሚሰበሰቡበት መንገድ ነው፡፡ ይህንን ዘዴ መጠቀም ያስፈለገበት ዋና ጉዳዩ
በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ላይ ሆኖ፣ ከነዚህ ደግሞ ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ስላሉን የተሻለ የመረጃ መሰብሰብያ ስለሆነ
ነው፡፡ በዚ መሰረት አምስት ክፍት ጥያቄዎች ማየት ከተሳናቸው ተጠኚዎችና ዓላማዎችና ጥያቄዎች በከፊል መረጃዎችን
ለማሰባሰብ ይሞከራል፡፡ በዚህም መንገዶች መረጃን በማሰባሰብ ጥናቱ ለታለመለት ግብ እንዲመታ ለማድረግ ይሞከራል፡፡
3.3.3 የቡዱን ውይይት
ይህ የመረጃ መሰብሰቢያ እውነታው የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን፣ ከመምህራን፣ ሰራተኞችና፣ አስተዳዳሪዎች በፅሁፋዊ መጠይቅ
መሰረት የተሰበሰቡ መረጃዎች ለማረጋገጥ የታለመለት ግብ እንዲመታ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ ይህንን የቡዱን ውይይት ዘዴ አራት
የትግርኛ ቋንቋ መምህራን ሶስት ሰራተኞች /ርእሳነ መምህራን/፣ የርእሰ መምህሩ ተወካይ የልማት ስራ አስከያጅ ሓላፊ፣
መምህራን አምስት የትምህርት ቤቱ አባላት በፅሑፋዊ መጠይቅ ያልተካተቱ አምስት የኔትዎርክ መሪዎች ባጠቃላይ ስምንት አካል
ጉዳተኛ ተማሪ ያቀፈ ነው፡፡
በሁሉቱ የትግርኛ መምህራን ጋር አምስት ክፍት ጥያቄዎች በማዘጋጀት በ 6/09/2011 ዓ/ም በአካል ጉዳተኞች የኔትዎርክ
መሪዎች ሰባት ክፍት ጥያቄዎች በማዘጋጀት 07/09/2011 ዓ/ም በፈረደ ረዳኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቡድን ውይይት
ተካሂዷል፡፡
በቡድን ውይይት የተገኙ ጥያቆዎች ለፅሑፋዊ ጥያቄዎች ከተማሪዎችና መምህራን የሚገኙ መረጃዎች የሚያጠናክሩና የጥናቱ
ለጥያቄዎቹና አላማዎችን መረጃዎችን በከፊል ለማግኘት ተችላል፡፡
3.3.4 ትዝብት
ይህንን ጥናት ትኩረት የአካቶ ትምህርት ደሰሳ አተገባበር በአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ስለሆነ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ባሉበት
በዘጠኛና አስረኛ ክፍል በትግርኛ ቋንቋ መማር ማስተማር በሳምንት ሁለት ጊዜ ለስድስት ቀናት ከ 1 -15/2011 ዓ/ም
ለአስራ ሁለት ክፍለ ጊዜ ክፍል ውስጥ በመጋት ትዝብት ተካሂዷል፡፡ በዚህ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ
አስር ማጠናከሪያ ነጥቦች በማዘጋጀት የአካቶ ትምህርት አዘገጃጀት ምን እንደሚመስል ተፈትሿል፡፡ በዚህኛውን መሰረት
የጥናቱን ጥያቄዎች፣ ዓላማዎች መረጃዎች በሙሉ ተሰብስባል፡፡
ይህ ጥናት በትንተናው ተተኳሪ መጠይቆች የተሰበሰቡትን የአካቶ ትምህርት ይዘቶችን ዳሰሳ አተገባበር ጥናቱ ገላጭ የምርምር
ዘዴን በመከተል የቀረቡትን ክፍትና ዝግ ጥያቄዎች መረጃዎች መሰረት በማድረግ የ 9 ኛና 10 ኛ ክፍል ትግርኛ ቋንቋ በሚለው
ጉዳይ የመምህራን ግንዛቤ ምን እንደሚመስል፣ መምህራን አካቶ ትምህርት እንዴት እንደሚያተግቡትን፣ በአካቶ ትምህርት
አተገባበር በመምህራንና ተማሪዎች ያጋጠሙ ችግሮች ምን እንደሆኑ በትግርኛ ቋንቋ መማር ማስተማር ሂዴት በተማሪዎች ላይ
ያላቸው ተፅዕኖ ለመዳሰስ፡፡ የፅሑፍ መጠይቅ፣ የቡድን ውይይት፣ ቃለ መጠይቅ፣ የብዱን ውይይትና ትዝብት በማካሄድ
መረጃዎችን ተገኝቶተዋል፡፡ በመሆኑም ትንተናው የሚካሄድበት አይነታዊና መጠናዊ የምርምር ዘዴ በመጠቀም ይካሄዳል፡፡